Genesis 16

አጋርና እስማኤል

1የአብራም ሚስት ሦራ፣ ልጆች አልወለደችለትም ነበር፤ እርሷም አጋር የምትባል ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። 2አብራምንም፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ልጅ እንዳልወልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጆች አገኝ እንደሆን ሄደህ ከአገልጋዬ ጋር ተኛ” አለችው።

አብራምም ሦራ ባለችው ተስማማ።
3አብራም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ሚስቱ ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋን አጋርን ሚስት እንድትሆነው ለባሏ ሰጠችው። 4አብራምም ከአጋር ጋር ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች። አጋርም ነፍሰ ጡር መሆኗን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን መናቅ ጀመረች። 5ሦራም አብራምን፣ “ለደረሰብኝ በደል ተጠያቂው አንተ ነህ፤ አገልጋዬ ዕቅፍህ ውስጥ እንድትገባ እኔው ሰጠሁህ፤ አሁን ግን ይኸው ማርገዟን ስታውቅ ትንቀኝ ጀመር፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) በአንተና በእኔ መካከል ይፍረድ” አለችው።

6አብራምም፣ “አገልጋይሽ እንደ ሆነች በእጅሽ ውስጥ ናት፤ የፈለግሽውን አድርጊባት” አላት። ከዚያም ሦራ ስላሠቃየቻት አጋር ጥላት ኰበለለች።

7 የእግዚአብሔር (ያህዌ) መልአክ አጋርን በአንድ የውሃ ምንጭ አጠገብ በምድረ በዳ አገኛት፤ ምንጩም ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ዳር ነበር። 8መልአኩም፣ “የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፤ ከየት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጃለሽ?” አላት፤

እርሷም፣ “ከእመቤቴ ከሦራ ኰብልዬ መምጣቴ ነው” ብላ መለሰች።

9 የእግዚአብሔርም (ያህዌ) መልአክ፣ “ወደ እመቤትሽ ተመለሽ፤ ለእርሷም ተገዥላት” አላት። 10ደግሞም መልአኩ፣ “ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር አይችልም” አላት።

11 የእግዚአብሔርም (ያህዌ) መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤

“እነሆ፤ ፀንሰሻል፤
ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ፤
እግዚአብሔር (ያህዌ) ችግርሽን ተመልክቷል፤
ስሙን እስማኤል
እስማኤል ማለት እግዚአብሔር ይሰማል ማለት ነው።
ትዪዋለሽ።
12እርሱም እንደ ዱር አህያ ይሆናል፤
እጁንም ባገኘው ሰው ሁሉ ላይ ያነሣል፤
ያገኘውም ሁሉ እጁን ያነሣበታል፤
ከወንድሞቹ ሁሉ ጋር እንደ ተጣላ ይኖራል።”
ወይም በስተ ምሥራቅ ይኖራል

13እርሷም ያናገራትን እግዚአብሔርን (ያህዌ)፣ “ኤልሮኢ” ብላ ጠራችው፤ ምክንያቱም “የሚያየኝን አሁን አየሁት”
ወይም ኋላውን አየሁት
ብላ ነበርና።
14ከዚህ የተነሣ የዚያ ምንጭ ስም፣ “ብኤርለሃይሮኢ”
ብኤርለሃይሮኢ ማለት የሚያየኝ የሕያው ምንጭ ማለት ነው።
ተብሎ ተጠራ፤ እስካሁንም በቃዴስና በባሬድ መካከል ይገኛል።

15አጋር ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ አብራምም ስሙን እስማኤል ብሎ ጠራው። 16አብራም፣ አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ ዕድሜው 86 ዓመት ነበር።

Copyright information for AmhNASV